በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19/2015፣ NBC ETHIOPIA-ዛሬ ማለዳ በኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን፣ በኦሮሚያ አከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ በኦሮሚያ ደንና የዱር እንስሳት ድርጅት አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ፖርኮችና የኢኮ ቱሪዝም ቦታዎች በጋራ ለማቋቋም፣ ለማልማትና ለማስተዋወቅ ሱባ ጥብቅ ደን ውስጥ በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ ተገኝቻለሁ።

ክልላችን በርካታ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች ቢኖረውም ማስተዋወቅና ማልማት ባለመቻሉ ከዚህ ሴክተር ማግኘት የሚገባንን ጥቅም ሣናገኝ ቀርተናል። በዚህም በርካታ የኢኮኖሚ፣ የባህል፣ ማህበራዊና ታሪካዊ ፋይዳዎችን አጥተን ቆይተናል።
ላላፉት ሶስት አመታት ይህንን ታሪክ ለመቀየር እንደ ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በተሰራው ስራ በቱሪዝም ዘርፍ ያሉንን እምቅ ሀብትና እድል የተረዳንበትና አሁንም በዚህ ዘርፍ ያለንን አቅም አሟጠን ከሰራንበት የምንፈልገውን ለውጥ ማምጣት እንደምንችልና በዘርፉ የህዝባችንን ተጠቃሚነት ለመጨመርና የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ ለመቀጠል በዛሬው ዕለት በሶስቱ ተቋሞቻችን መካከል የተደረገው መግባባት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ።
ሶስቱ ተቋሞቻችን በተፈጥሮ ሀብቶቻችን ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ለመታደግና ሀብቱን ጥቅም ላይ ለማዋል በ12 ዞኖች ውስጥ የሚገኙ ከ500 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የተከለሉ ፓርኮችንና 18 በ117 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተከለሉ የኢኮ ቱሪዝም ስፍራዎችን በጋራ ለማልማትና ለማስተዋወቅ የጋራ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን፣ በዚህ ረገድ የሚሰራው ስራ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን በመጠቀም የስራ እድል በመፍጠር የህዝባችንን ኢኮኖሚ ከመደገፍ ባሻገር የተፈጥሮን ሚዛን በመጠበቅ የህዝባችንን ባህል፣እሴትና ማንንት በመመለስ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው በመሆኑ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስራውን የሚደግፍና አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ ለማድረግ ከፍተኛ ቁርጠኝነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












