በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19/2015፣ NBC ETHIOPIA- አሁናዊውንና ወቅታዊውን ዓለም አቀፍ ፈተናዎች ለመፍታት ፓን አፍሪካኒዝም ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ በፓኪስታን የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀማል በከር ገለጹ፡፡

አምባሳደር ጀማል በከር በፓኪስታን ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በፓን አፍሪካኒዝም ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ላይ በፖኪስታን ኢስላማባድ መክረዋል።
በውይይቱ አምባሳደር ጀማል በከር ፓን አፍሪካኒዝምን ማስፋፋት በአሁን ሰአት እየተከሰቱ ያሉ እንደ አየር ንብረት ለውጥ፣ ሽብርተኝነት፣ ስደትና የአለምን ኢኮኖሚ ውስብስብ ችግሮች ለመፍታት ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን አብራርተዋል።
አምባሳደር ጀማል የአፍሪካን የጋራ ጥቅሞች በአለም አቀፍ መድረክ በጋራ ድምጽ ማስተጋባትና ማስተዋወቅ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
እንደ ኢ ፕ ድ ዘገባ በውይይቱ የተገኙት የአፍሪካ ሀገራት የሚሲዮን መሪዎች የአፍሪካን አንድነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸው ለጋራ ጥቅሞች ተቀራርበው ለመስራት መስማማት ላይ ደርሰዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc












