በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19/2015፣ NBC ETHIOPIA-አሜሪካ ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት የነበረው አውሮፕላን ከምድር ወደ ሰማይ በሚወነጨፍ ሚሳኤል ተመትቶ ወድቋል የሚለው ትንተና የሚያስኬድ አይደለም እያለች ነው።

ፔንታጎን ክስተቱን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ ምናልባት አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ተጠምዶበት የነበረው ቦምብ መፈንዳቱን ተከትሎ ነው ሊሆን ይችላል ብሏል።
የቅጥረኛ ቡድኑ ቫግነር መሪ ዬቭጌኒ ፕሪጎዥን ተሳፍሮበት የነበረው አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወቱ ሳያልፍ አይቀርም መባሉን ተከትሎ በርካቶች ለአውሮፕላኑ መከስከስ ምክንያት ነው ያሉትን መላምት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ የአሜሪካ መከላከያ ቃል አቀባይ ብርጋዲዬር ጀነራል ፓትሪክ ራይደር የአውሮፕላኑን መከስከስ ተከትሎ የዋግነሩ መሪ የመሞት ዕድል ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው አውሮፕላኑ ግን በሚሳኤል ተመትቶ ወድቋል የሚለው እውነት የመሆኑ ዕድል ጠባብ ነው ብለዋል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












