አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ውስጥ ኢንዱስትሪን ለማሳደግ ሲሰራ የነበረውን የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት አቅምን ለማሳደግ በዘርፉ ላይ ከተሳተፉ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አክሊሉ ታደሰ የኢንዱስትሪ ፖርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አከናውናቸዋለሁ ካላቸው ሪፎርሞች መካከል የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ን ማሳደግ ና አብሮ መስራት መሆኑን አንስተዋል።

የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች አገልግሎት ምስረታውን በ1975 ዓ.ም ያደረገ ሲሆን አላማውም በኢትዮጵያ ሊሰሩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን የሚጠቁም፣ ጥናት የሚያረግ ና ወደ ተግባር ለማስገባት የሚረዳ መሆኑ ተነስቷል።
ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












