አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17/2015 ፣ NBC ETHIOPIA -የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ “ሄጂሞኒዝም ወይም ጠቅላይነት በቻይና ዘረ መል (ዲ ኤን ኤ ) ውስጥ የለም ፤ ፍትሃዊ እና እኩልነት የሰፈነበት ዓለምአቀፍ ስርአት ለመገንባት እንደምትፈልግና የብሎክ ወይም የጎራ ግጭትን እንደማትቀበል በብሪክስ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል ።

ፕሬዝዳንት ዢ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በተካሄደው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ሲጀመር ነበር ይህን ንግግር ያደረጉት ፡፡ ቻይና በትክክለኛው የታሪክ ጎራ ላይ ቆማለች እናም ለጋራ ጥቅም ና ፍትሃዊ ነት ለማረጋገጥ እንደምትሰራ እና ብሪክስ “ምንም ዓይነት ተቃውሞ ሊገጥመው ይችላል ነገር ግን ከማደግ ምንም የሚያግደው ነገር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/