
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2015 ፣ NBC ETHIOPIA – የማንችስተር ሲቲ ተከላካይ ጆን ስቶንስ በጉዳት ሳቢያ እስከ መስከረም ወር ድረስ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ ተረጋግጧል።
የክለቡ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ፣ ስቶንስ በቀጣይ ከሸፊልድና ፉልሃም ጋር በሚያድርጓቸው የሊጉ ጨዋታዎች አገግሞ እንደማይሰለፍ አስታውቀዋል።
እንግሊዝ በዩሮ 2024 ማጣሪያና በወዳጅነት ጨዋታዎች ከዩክሬንና ስኮትላንድ ጋር ለምታደርጋቸው ግጥሚያዎችም እንዲሁ። በቅድመ ውድድር ዘመን ልምምድ ላይ ቀላል የዳሌ አጥንት ጉዳት ያስተናገደው ተጨዋቹ ሲቲ ባደረጋቸው ያለፉ ሶስት ጨዋታዎች ላይ አልተሰለፈም ነበር።
በዐቢይ ሀብታሙ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc












