
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2015 ፣ NBC ETHIOPIA “የምስራቅ አፍሪካ አትሌቶች ጽናትና አይበገሬነት የድሉን ደስታ በጋራ እንድናከብር አድርጎናል” ሲሉ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ገለጹ።
በሃንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ያለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ሶስተኛ ቀኑን ይዟል።
የኢጋድ አባል አገራት አስደናቂ አትሌቶች እያስመዘገቧቸው ባሉ ድሎች መደሰታቸውን ዶክተር ወርቅነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል። “አትሌቶች ለማሸነፍ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣አይበገሬነትና ስፖርታዊ ጨዋነት በቀጣናው ተነሳሽነት የፈጠረና ድሉንም ደስታውንም በጋራ እንድንካፈል አድርጓል” ብለዋል፡፡
እንደ ኢዜአ ዘገባ ከትናንት በስቲያ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣አትሌት ለተሰንበት ግደይና አትሌት እጅጋሁ ታዬ ከእንድ እስከ ሶስት በመውጣት ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












