
ዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15/2015 ፣ NBC ETHIOPIA -የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ የምስራቅ ዕዝ ሠራዊት በቅርቡ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና በጅግጅጋ ከተማ የገበያ ማዕከል ላይ በተከሰተው የእሳት አደጋ ሀብት ንብረታቸው ላጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከተ።
በተጨማሪም በኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል መሀመድ ተሰማ፤ ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመር አስረክበዋል።
በዚህም ሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የህዝብ ሰላምና ደህንነት ከመጠበቁ ባሻገር በክልሉ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች የሚደረሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የድርሻውቸውን በመወጣታቸው፣እጅግ የሚያመሰግን ሰናይ ተግባር ነው ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
የሶማሌ ክልል መንግሥት በጅግጅጋ ከተማ የገበያ ማዕከል ላይ በተፈጠረው የእሳት አደጋ ሀብታቸው የወደመባቸው ወገኖች ለመርዳት በአገር ውስጥና በውጪ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ በተገቢው ሁኔታ እየተሰራ መሆኑንም ተገልጿል።
በመጨረሻም በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ጄኔራል መሀመድ ተሰማ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ኡመር ፣የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴው አባል አቶ ጠይብ አህመድ-ኑር እንዲሁም የምስራቅ ዕዝ መኮንኖችን መገኘታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc