አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA – ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሞስኮ ተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት ደርሶበታል፡፡

የሩሲያ ባለስልጣናት የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላን በአየር መከላከያ ተመትቶ በመውደቁ ፍርስራሹ በከተማው ማዕከል ላይ ጉዳት ማድረሱን አሰታውቀዋል ። የዩክሬን ባለስልጣናት ግን እስካሁን ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት ያሉት ነገር የለም።
የሞስኮ ቭንኮቮ አየር ማረፊያ ከጥቃቱ በኋላ በጊዜያዊነት አገልግሎት ያቋረጠ ሲሆን ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ድጋሚ ተከፍቶ አገልግሎት መጀመሩ ተገልጿል።
እስከ ብዙ ጊዜ ድረስ ሞስኮ በዩክሬን ጦር ጥቃት ደርሶባት አያውቅም ነበር። ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሞስኮ የድርን ሰለባ እየሆነች መጥታለች፤ ባለፈው ግንቦት እንኳን 30 የሚሆኑ ሕንፃዎች በተደጋጋሚ የድሮን ጥቃት መጎዳታቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስታውቋል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -facebook.com/ethiopiannbc












