አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA- የግብረሰዶም ወንጀል በኢትዮጵያ ባህልና ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው ድምፅ አልባ ትውልድ ገዳይ ተግባር መሆኑን ስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም ትውልድን ከግብረሰዶም እንታደግ ማህበር አስታወቀ::

ትውልድ እንዳይቀጥል ዘር እንዳይተካ የሚያደርገውን ወንጀል በማጥፋት ጉዞ ውስጥ የሃይማኖት አባቶች በርካታ የቤት ሥራዎች ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል::
የማህበሩ መሥራችና ፕሬዚዳንት ሊቀ ትጉሃን መምህር ደረጀ ነጋሽ ዘወይንዬ እንደተናገሩት፤ ማንነትንና እሴትን የመርሳት ውጤት የሆነውና በአንዳንድ ሀገራት እየተቀነቀነ የመጣው የግብረሰዶም ወንጀል በኢትዮጵያ ባህልና ሃይማኖት ተቀባይነት የሌለው ድምጽ አልባ ገዳይ ተግባር ነው::
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ጉዳዩን በመቃወም ሥራዎች ሲሰሩ መኖራቸውን ያወሱት መምህሩ፤ በየጊዜው እየተስፋፋ የመጣውና ሕገወጡ የግብረሰዶም ድርጊት የዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውጤት ነው ብለዋል::
መምህር ደረጀ እንዳሉትም፤ የግብረሰዶም ተግባር ከአጸያፊነቱም ባሻገር በሽታን የሚያመጣ ሲሆን፤ ሰዎችን ለአላስፈላጊ ድብርትና ራስን እስከ ማጥፋት የሚያደርስና ትውልድን አምካኝ ነው::
በእስልምናም ይሁን በክርስትና እምነት በማይደገፍበት ሁኔታ ከ97 በመቶ በላዩ ህዝቧ ሃይማኖተኛ በሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ የዘመናዊ ቅኝ ግዛት ውጤት የሆነው ጎጂ ልማድ ሊሰማባት አይገባም።
መንግሥትም ወንጀሉ ላይ ያሉ ሕግና መመሪዎችን በማጥበቅና የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት አስተዳደራዊ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ትውልድን መታደግ ይገባዋል ሲሉ መምህር ደረጀ መግለጻቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧል ::
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc












