አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA -ቱሪዝም ሚኒስቴር በትግራይ ክልል በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በነበረው ግጭት ምክንያት ቆሞ የነበረውን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ዳግም ለማነቃቃትና ለማስጀመር የሚያስችል ስልጠና በመቀሌ ከተማ እየሰጠ ይገኛል።

በፕሮግራሙ ማስጀመሪያ መርሀግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ዶ/ር ኃላፊ አፅብሐ ገብረ እግዚሐብሄር ከነበሩ ችግሮች በኋላ እንደዚህ አይነት መድረክ ሲዘጋጅ የመጀመሪያ መሆኑን ጠቅሰው ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ይህን የስልጠና መድረክ በማዘጋጀቱና ከጎናችን በመሆኑ ምስጋናችን የጎላ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ስለሽ ግርማ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አፅብሐ ገ/እግዚሐብሄር፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝተዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/












