አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 12/2015፣ NBC ETHIOPIA – በዉይይይ መድረኩ ላይ ቢሮ ባሳለፍነዉ ዓመት ከተማዋ ዘመናዊ፣ ፍትሀዊና ተወዳዳሪ የንግድ ማዕከል ከሆኑ የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደም ከተማ ሆና መገኘት እንድትችል ስሰራ ቆይቻለሁ ሲል ገልጿል።

አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ የዳቦ ዝቅተኛዉ ግራም 70ግ እንዲሆን ማድረግ፣ የምርት ጥራት ለማረጋገጥ ምርመራ ለማድረግ አሰራር መዘርጋት፣ በገበያ ማዕከላት ላይ የሚታዩ ህገወጥ ስራዎች ማረም እንዲሁም እለታዊ የገበያ ዋጋ መረጃን ማጋራት ይጠቀሳሉ።
በተጨማራም በአዲስ አበባ ከተማ እህል በረዳ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 5749 ኩንታል ጤፍ ተወርሶ ለሸማቾች የህብረት ስራ ማህበር በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያስረክቡ ተደርጓል።
የተጀመሩ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ቢሮ አዳዲስ ዕቅዶችን ለ 2016ዓ.ም አቅርቦ እንዲፀድቁ ዉይይት እያካሄደም ነዉ።
በሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc