ከህብረተሰቡ በመጣ ጥቆማ በቦሌ ክ/ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ መጠጥ ቤቶች በተደረጉ ጥናቶችና ጥናቶቹን መሰረት ተደርገው በተከናወኑ የኦፕሬሽን ተግባራት በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ገንዘቦች መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ውስኪ ቤቶቹ በህጋዊ የንግድ ሽፋን ስም በጥቁር ገበያ የገንዘብ ምንዛሬ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደነበርም መረጋገጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያሳያል፡፡
ከተያዙት ገንዘቦችም ውስጥ 2 ሚሊዩን 916 ሺ 800 የኢትዮጵያ ብር፣ 54 ሺ181 የአሜሪካ ዶላር፣ 34 ሺ 50 ዩሮ፣ 305 የእንግሊዝ ፓውንድ፣ 7 ሺ 719 የሳውዲ ሪያል፣ 11ሺ440 ድርሀም፣ 52 ሺ የሊባኖስ ፓውንድ፣ 80 ሺ640 የሱዳን ፓውንድ እንዲሁም የተለያዩ ስድስት ሀገራት የገንዘብ ኖቶች ተይዘዋል፡፡
በህጋዊ የንግድ ስራ ሽፋን ተሰማርተው መሰል የወንጀል ተግባራት ውስጥ የሚገቡ የንግድ ተቋማት ላይ በጥናት ላይ የተመሰረተ የወንጀል መከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ሲል አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












