
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA- በምዕራብ አፍሪካ ኬፕ ቨርዴ ባህር ዳርቻ ስደተኞችን አሳፍራ የነበረች ጀልባ ተንሳፋ ከተገኘች በኋላ ከ60 በላይ ስደተኞች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተገልጿል።
ሕጻናትን ጨምሮ 38 ሰዎች ከሞት የተረፉ ሲሆን በሳል ደሴት ላይ እርዳታ ሲደረግላቸው በሚንቀሳቀሱ ምስሎች ታይተዋል።
በጀልባ ላይ የነበሩት ሁሉም ስደተኞች ከሴኔጋል የተነሱ መሆናቸው ታውቋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ አደጋውን አስመልክቶ የወጡ ሪፖርቶች አንደጠቆሙት ጀልባዋ ሰምጣ እንደነበርና በኋላ ላይ ተንሳፋ መገኘቷን አመልክተዋል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












