
አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA-የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በቻይናው የፋይናንስ ምክትል ሚኒስትር ሊያው ሚን የተመራ ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
የውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካለል ያለው የኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ ኢኮኖሚያዊ እድገት ማምጣት እንደ ሆነ ተጠቁሟል፡፡
ኢንደስትሪላይዜሽንን ለማምጣት ከፖሊሲ እና ስትራቴጂ ዝግጅት ጀምሮ ከቻይና መልካም ተሞክሮዎችን ወስደናል ያሉት የኢንዱትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ዘላቂና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣትም የግሉን ዘርፍ ለመደገፍ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የግልን ዘርፉን የሚያበረታታና ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የኢንቨስትመንት ትስስር የሚያጠናክር ፖሊስን ጨምሮ እንደ ሀገር በርካታ የኢንቨስትመንት መደላድሎች እንዳሉ ጠቅሰው፣ አቅም ያላቸው አዳዲስ ባላሃብቶችን በመሳብ፣ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ምጣኔ ሃብት ሚዛናዊ በማድረገ፣ የሁለትዮሽ ንግድ ግንኙነት ማጠናከር እና የተለያዩ የመሰረት ልማት ድጋፎችን የቻይና መንግስት እንዲያደርገ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc












