አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11/2015፣ NBC ETHIOPIA የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር በአልሸባብ አሸባሪ ቡድን ላይ ወታደራዊ ጥቃት ከመጀመሩ በፊት በማእከላዊ ጋልሙዱግ አካባቢ ባለው የሽብር ቡድን ላይ ጥቃት መክፈቱን አስታውቋል ።

በሙዱድ እና በጋልጉዱድ አካባቢዎች ላይ የተቀበሩ ፈንጂዎችን በተሳካ ሁኔታ ማጽዳት መቻሉንና ለዜጎች ደህንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን የሶማሊያ መከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
በሂራን ግዛት በማሃስ ወረዳ የሰፈሩት ወታደሮች በአልሸባብ የአሸባሪዎች መሸሸጊያ ቦታዎች ላይ ያነጣጠረ የተሳካ ዘመቻም ማድረጋቸውን የጦሩ መግለጫ ያመለክታል ።
በሞቃዲሾ የፀጥታና ደህንነት ሀላፊ የሆኑት አህመድ አዳን ጦራቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ አሸባሪዎችን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በወሰደው እርምጃ በርካታ ጥቃቶችን ማክሸፍ እንደቻሉ መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












