
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 5 2015| NBC ETHIOPIA የዩክሬን የባህር ኃይል አባላት ከሩሲያ የሚቃጡ ከባህር የሚወረወሩ ፈንጂዎች በሁሉም የመርከብ መስመሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ማስጠንቀቃቸው ታውቋል ፡፡
ዩክሬን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ በወደቦቿ ተከማችተው የሚገኙ የጭነት መርከቦችን ለመልቀቅ በጥቁር ባህር ላይ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል መንገድ እንደምትከፍት አስታውቃለች።
ሐሙስ ዕለ እንዲከፈት የተደረገው መተላለፊያ መስመር ከየካቲት 2022 ከሩሲያ ወረራ ጀምሮ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችተው የነበሩ እህል የጫኑ ኮንቴይነሮች ሳይንቀሳቀሱ ቆይተዋል ፡፡
በጦርነቱ ምክንት ወደቦቹ ተዘግተው መቆየታቸው የሚታወስ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል ፡፡
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc