አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4 2015| NBC ETHIOPIA – የቻይና ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዓለም ላይ ተመራጭ ከሆኑ የጎብኚ መዳረሻዎች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ኢትዮጵያን እንዲጎበኟትም ለዜጎቹ ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።
ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች መጎብኘት ይገባቸዋል ካላቸው ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንደኛዋ ሀገር መሆኗን በመግለጫው አንስቷል።

ሚኒስቴሩ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ቻይናውያን ሊጎበኟቸው ይገባል ያላቸውን ሀገራት ዝርዝር ያወጣ ሲሆን፥ በተለያዩ ኤጀንሲዎች አማካኝነት የጉብኝት የሙከራ መርሐ ግብር መጀመሩንም አስታውቋል።
መርሐ ግብሩ ቻይና ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን የቱሪዝም ትብብርና ተሳትፎ የበለጠ በማስፋት ረገድ አዎንታዊ ሚናው ከፍ ያለ እንደሆነምነው የገለጸው።