
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4 /2015 | NBC ETHIOPIA- ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ ግንኙነት ውጤታማ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ መከወኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም፤ በውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚህም ባለፈው ሳምንት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር፣ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሺማሳ ሃያሺ እና የደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ ግንኙነት ውጤታማ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማከናወኗ ተጠቅሷል።
ይህ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ በ2016 በጀት ዓመትም የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራም ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc