አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4 /2015 | NBC ETHIOPIA- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ድጋፍ በጋምቤላ ከተማ በ110 ሚሊዮን ብር እየተገነባ ያለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ እየተገባደደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ኢዜአ ባደረገው ጉብኝት እንደገለፀው ትምህርት ቤቱ የሁለቱን ክልል ህዝቦች ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ዓላማ ተደርጎ እየተገነባ ያለ ትምህርት ቤት መሆኑን አስታውቋል፡፡
የትምህርት ቤቱ ግንባታ ፕሮጀክት የቴክኒክ ተቆጣጣሪ አቶ ታመነ ሳህሉ በወቅቱ እንዳስረዱት፤ ትምህርት ቤቱ ለ2016 የትምህርት ዘመን አገልግሎት እንዲሰጥ ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሚገኝ እና ግንባታው 98 በመቶ መድረሱን አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለማስረከብ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።

የኦሮሚያ፣ የጋምቤላና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሰላምና የልማት የጋራ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ኮት ቻም በበኩላቸው፤ ትምህርት ቤቱ በተለይ በክልሉ የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ለተነደፈው ግብ መሳካት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc










