አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4 /2015 | NBC ETHIOPIA-በሀዋይ ማዊ ግዛት በደረሰ ሰደድ እሳት በትንሹ 36 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ።

እሳቱ በሚያልፈው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ተገፍቶ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሕንፃዎችን በማውደም አንዳንዶችንም ወደ መሬት ጥሎዋል።
በማዊ ደሴት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው ለመውጣት የተገደዱ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም ታውጇል። ከፍተኛ የአሰሳ እና የማዳን ስራ እየተካሄደ ሲሆን ሄሊኮፕተሮችም ውሀ ከላይ ሆነው በእሳቱ ላይ እያርከፈከፉ ይገኛሉ።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc











