
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2 /2015 | NBC ETHIOPIA- የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2015 በጀት አመት የእቅድ የአፈጻጸም እና የ2016 በጀት የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሪፖርት በማቅረብ ላይ ይገኛል።
በ2015 በጀት 37.7 ቢሊዮን ብር ለማግኘት አቅዶ 35.5 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጻል።
ገቢው የተገኘው ከኤሌክትሪክ ሽያጭ እና አዳዲስ ደንበኞችን በማገናኘት ነው ብሏል።
በ2015 በጀት አመት ከመሰረተ ልማት ማስፋፋት እና ማዘመን አንጻር ወደ ትግበራ የገቡ ፕሮጀክቶች አሉ ያለው አገልግሎቱ በ 6 ክልሎች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው ብሏል።
በሰብለ ወንድማገኝ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












