
የምዕራብ አፍሪካ አባል ሀገራት ስብስብ የሆነው ኤኮዋስ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ፕሬዝደንት ሞሐመድ ባዙም እስከ ትናንት እሁድ ከእስር ተለቀው ወደ ስልጣናቸው ካልተመለሱ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጾ ነበር ።
በሌላ በኩል የጁንታው ቃል አቀባይ የኒጀር ጦር ሠራዊት ሀገሪቱን ለመከላከል በተጠንቀቅ ሆነው እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
ፕሬዝደንት ባዙም ሐምሌ እኤአ 19/2023 በጁንታው በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ ጀኔራል አብዱራህማኔ ቺያኒ አዲሱ የሀገሪቱ መሪ ሆነው ታይተዋል።
ፈረንሳይ፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት እና ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የመንግሥት ግልበጣውን እንዳልተቀበሉት አልጀዚራ ዘግቧል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









