
ዶክተር ሳሙኤል ተፈራ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ብሪክስ ውስጥ ያሉ ሀገራት ከዓለም ኢኮኖሚ 31 ነጥብ ሰባት በመቶ የሚሆን ድርሻ አላቸው። በዚህም ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ከቻለች ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያስችላል።
እንደ ኢ ፕ ድ ዘገባ የብሪክስ አባላት ከ30 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ዓመታዊ GDP ያላቸው ሀገራት ናቸው ያሉት ዶክተር ሳሙኤል በመሆኑም ሦስት ቢሊዮን የሚጠጋ የዓለም ሕዝብ የሚኖረው በኅብረቱ ሀገራት ውስጥ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን ሕዝብ፣ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ መሆን፣ በአፍሪካ ቀንድ የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካዊ አቀማመጥና በቀጣናው ያላት ተፅዕኖ ፈጣሪ ናት። በዚህም በአባል ሀገራቱ ጥያቄዋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ዕድል ይሰጣታል ሲሉ ዶክተር ሳሙኤል ተናግረዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት










