
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በየጊዜው መልካቸውን እየቀያየሩ የሚስተዋሉት አለመግባባቶች መፍተሄ የሚያገኙት ቁጭ ብሎ በመነጋገር ነው የሚሉት የሃይማኖት አባቶቹ ለዚህም አገራዊ ምክክሩ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የህዝብ ወኪሎችና የፖለቲካ ልሂቃን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ በተለይ የሃይማኖት አባቶች ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በመስራት ምክክሩ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከናወን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ነው የተገለጸው፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ጽሀፈት ቤት የስብከተ ወንጌል እና ሃዋሪያዊ ተልዕኮ መምሪያ ዋና ሃላፊ መልዕከ ሰላም ዶክተር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ፤ ህብረተሰቡ በምክክሩ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆን የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማትና ተራድኦ ዘርፍ ኋላፊ ሼህ ዛኪር ኢብራሂም በበኩላቸው በእስልምና አስተምህሮ ሰላምን መመካከርንና አንድነትን በጽኑ ያስተምራል ብለዋል፡፡
የኮሚሽኑ መቋቋምና ወደ ስራ መግባት በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚያደርግ በመሆኑ ትልቅ ትርጉም አለው ሲሉም አክለዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች የኮሚሽን አባላቱ ለሚያቀርቡት ሃሳብ እና ለሚያስፈልገው ሂደት ሁሉ መተባባር እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
እንደ ኢፕድ ዘገባ፤ በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን የትምህርት ክፍል ኋላፊ አባ ዳንኤል ሃሶ፤ ኮሚሽኑ እስካሁን በመጣበት ሂደት ሁሉ የሃይማኖት አባቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ማሳተፉን ተናግረዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












