
ከ6.5 ቢሊዮን ህዝብ መካከል ፣ ከአምስት ሰዎች አራቱ የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዳደረሰባቸው አዲስ ጥናት ማመልክቱን አናዶሉ ዘግቧል።
በፕሪንስተን ኒው ጀርሲ የሚገኘው የሳይንስ ኮሙኒኬሽን ቡድን የሆነው ክላይሜት ሴንትራል ዘገባ ፣ በሀምሌ ወር የዓለም ከፍተኛ የሙቀት ሪከርድ መመዝገቡን ገልጿል። ሪፖርቱ በ 200 አገሮች ውስጥ በ 4,700 ከተሞች ውስጥ በየቀኑ የሙቀት መጠን ተንትኗል ።
ውጤቱ እንደሚያሳየው በዓለም ዙሪያ ቢያንስ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች “በሀምሌ ወር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከፍተኛ ተጽዕኖ ደርሶባቸዋል ።
የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመቀነስ እና ሰዎች በየዓመቱ በከፍተኛ ሙቀት እንዳይሞቱ ለመከላከል ስልቶች መኖራቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website -https://nbcethiopia.com/news/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












