
ኢዜአ እንዳስታወቀው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀያሺ ዮሺማሳን ተቀብዬ አነጋግሪያለው።
ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች:: በሁለቱ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመተባበር ቁርጠኛ አቋምም አላት” ብለዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://nbcethiopia.com/news/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









