
በውይይቱ የመደመር እሳቤ ለሰላም፣ ለልማት እንዲሁም ለብልጽግና መረጋገጥ ያለው ሚና ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል። በሌላ መልኩ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር በሚያስችሉ ሃሳቦች ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መታደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://nbcethiopia.com/news/
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት










