
በትልቁ የአባይ ወንዝ ላይ በባህር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የአባይ ድልድይ ግንባታ 98 በመቶ መድረሱን ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘው መረጃ ይጠቁማል፡፡

በቻይናው ሲሲሲ ኩባንያ የተገነባው ድልድይ ሙሉ በሙሉ ግንባታው ለማጠናቀቅ የቀረው ወደ ድልድዩ የሚያስኬዱ ተያያዥ መንገዶች ግንባታ ብቻ መሆኑን በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የፕሮጀክቱ ኢንጂነር ለሚ በቀለ ለኤን ቢ ሲ ተናግረዋል፡፡
በሔርሜላ ፍቃደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












