
አፍሪካ ያላት እምቅ አቅም የታወቀ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ የአፍሪካ አመታዊ የጂዲፒ እድገት ላለፉት 20 አመታት አራት እና አራት ነጥብ አምስት በመቶ ሲሆን፤ ይህ የእድገት መጠን ከዓለም እድገት መጠን የበለጠ መሆኑን ነው የጠቀሱት።
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የንግድና የሰብአዊ ግንኙነቶች ይበልጥ ማሳደግ እንደምትፈልግም ነው ፕሬዝዳንት ፑቲን የተናገሩት።
ሩሲያ ባለፉት ሁለት አመታት ለአፍሪካ አገራት የምትልከውን ነዳጅ፣ የነዳጅ ውጤቶችና የተፈጥሮ ጋዝ በሁለት ነጥብ ስድስት እጥፍ መጨመሯን ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል።
ከንግድ በተጨማሪም ሩሲያ በኃይል ልማት መስክ ሶስት ነጥብ ሰባት ጊጋ ዋት አቅም ያላቸውና በተለያዩ የግንባታ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ 30 ፕሮጀክቶችን በ16 የአፍሪካ አገራት ውስጥ እያከናወነች መሆኗን ፕሬዝዳንተ ፑቲን ገልጸዋል።
በቅርቡም በግብጽ ስዊዝ ካናል አካባቢ የሩሲያ ኢንዱስትሪ ዞንን ለመክፈት ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጋር መነጋገራቸውንም ፕሬዝዳንት ፑቲን ጠቅሰዋል።
የአፍሪካ አገራት በግብርናው መስክ ያላቸው አቅም ራሳቸውን መመገብ ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ዓለምም መትረፍ የሚችል ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን፤ አፍሪከ ዘርፉን ለማዘመን የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፉም ቃል ገብተዋል።
ሩሲያ እኤአ በ2022 11 ነጥብ አምስተ ሚሊዮን ቶን ጥራጥሬ ለአፍሪካ አገራት ማቅረቧን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቱ፤ በተያዘው አመት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ 110 ሚሊዮን ቶን ያህል እህል ለአፍሪካ ማቅረቧንም ተናግረዋል።
በቀጣዮቹ ሶስታና አራት ወራትም ለቡርኪናፋሶ፣ ዝምባብዌ፣ ማሊ፣ ሶማሊያ፣ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና ኤርትራ ከ25 ሺህ እስከ 50 ሺህ ቶን ጥራጥሬ በነጻ ለመስጠት ሃገራቸው ዝግጁ መሆኗን ማስታወቃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website –https://nbcethiopia.com/news/