
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና 20 ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች በሸገር ከተማ ገዳ ፋጂ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰጀምረዋል፡፡ በ24 ሚሊየን ብር ወጪ የወረዳውን ትምህርት ቤት በማደስና የአስር አቅመ ደካሞች ቤቶች እድሳት ይካሄዳል።የጠቅላይ ሚኒስትር የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ መኪዩ ሙሀመድ በመርሃግብሩ ላይ እንደገለጹት፡-በአገር አቀፍ ደረጃ በርካታ ኢኒሼቲቮች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡ ከዚህም የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ ነው፡፡

በአንድ ወር እድሳታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቁ ገልጸው ለተማሪዎች የደብተርና ቦርሳ ስጦታ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ የአስር አቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤቶችና የትምህርት ቤት እድሳትን በማስጀመር የችግኝ ተከላ ተካሂዷል፡፡ በመርሃግብሩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትና 20 ተጠሪ ተቋማት አመራሮች መገኝታቸውን ኢ ፕ ድ ዘግቧዋል፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopi
Facebok- https://www.facebook.com/ethiopiannbc












