
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia- የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በአግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ ቱሪዝም እና ኢ-ኮሜርስ ላይ በሚታዩ ችግሮች ዙሪያ ከመንግስትና እና ከግሉ ዘርፍ ጋር የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል።

በሀገሪቱ የኢኮኖሚ ብዝሀነት እና የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትልቅ ድርሻ ያላቸውን የግብርና፣ ቱሪዝም እና የኢ-ኮሜርስ ዘርፎችን ለማነቃቃት እና ለማጠናከር በሚል ነው ውይይቱ እየተካሄደ ያለው ።
በሀገራችን የኤሌክትሮኒክስ ግብይት እየተስፋፋ ቢሆንም የኢንቨስትመንትና ፋይናንስ አቅርቦት አለመኖር፣ ምቹ የክፍያ ስልቶችና አሰራሮች ክፍተት፤ የክፍያ ስርአት ቅንጅት እጥረት እና የኢንተርኔት መሰረተ ልማቶች ደረጃቸውን አለመጠበቃቸው በዘርፉ ላይ ማነቆ እየሆኑ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዝዳንት መላኩ እዘዘው ተናግረዋል።

በምክክር መድረኩ የኢንዲስትሪ ሚኒስቴር፣ የግብርና ፣ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ፣ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፋበት ነው።
በሀሴት ሀይሉ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












