አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia- የትዊተር ባለቤት ኢላን መስክ የትዊተር ሎጎ ከሚታወቅበት የወፍ ምልክት ወደ ኤክስ [X] ሊቀይር መሆኑን ገልፃል።

የትዊተር አርማ የሆነችው ወፍ እንደምትቀየር ያሳወቀው መስክ “በቃ ሁላችንም የትዊተር አርማን ቻው የምንልበት ጊዜ ተቃርቧል። ቀስ በቀስ ደግሞ ሁሉንም ወፎች” ብሏል።
የዛኑ ዕለት አዲስ ጊዜያዊ አርማ ይፋ እንደሚደረግም ያሳወቀው መስክ የእንግሊዝኛ ኤክስ ፊደል ምልክት ያለበት አርማ ለጥፏል።
የትዊተር ሥራ አስፈፃሚ ሊንዳ ያካሪኖ በትዊተር ገፃቸው አርማ መቀየሩ አስደሳችና አዲስ ጅማሮ ነው ብላለች።
የትዊተር ድረ-ገፅ እንደሚለው ሰማያዊ ቀለም ያላት ወፍ “እጅግ ልዩ የሆነች ንብረታችን ናት። ለዚህ ነው የምንጠብቃት።”
ኩባንያው ባለፈው ሚያዚያ ለአጭር ጊዜ አርማውን ዶጅኮይ በተሰኘው ክሪፕቶከረንሲ አርማ ቀይሮ እንደነበር ይታወሳል።
ነገር ግን ኢላን መስክ በኋላ የዶጅኮይን ዋጋ ከፍ እንዲል አድርጓል በሚል ከክሪፕቶከረንሲ ኢንቨስተሮች ወቀሳ ደርሶበት ነበር።
መስክ፤ በያዝነው ወር መባቻ የትዊተር ተጠቃሚዎች በቀን ማየት የሚችሉት ‘ትዊት’ ይገደባል ማለቱን ተከትሎ ተጠቃሚዎች አመፅ ቀስቅሰው እንደነበር አይዘነጋም። ኢላን መስክ ትዊተር ከገዛው በኋላ ኩባንያው ከግማሽ በላይ ሠራተኞችን አባሯል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












