አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከጣሊያን አቻቸው ኤድሞንዶ ቺሬሊ ጋር ተወያዩ።

ውይይታቸውም በዋናነት የሁለቱ አገራት ግንኙነት በሚጠናከርበት ጉዳይ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በዚህም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ረጅም ዘመናት ያስቆጠረ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር አገራቱ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር ያላትን ሁለንተናዊ የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደምትሻ አምባሳደር ብርቱካን ተናግረዋል። ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከር እያከናወነች ያለውን ስራም አድንቀዋል።
የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኤድሞንዶ ቺሬሊ በበኩላቸው ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብሯን ይበልጥ የማጠናከር ፍላጎት አላት ብለዋል።
የሽብርተኝነት እንቅስቃሴን በመታገልና ህገ ወጥ ስደትን በመከላከል ረገድ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።
በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት የጣሊያን እገዛ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ኢ ፕ ድ ገልጻል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc










