አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia- ቻይና ቺን ጋንግን በውጪ ጉዳይ ሚኒስትርነት ከተሾሙ ሰባት ወራት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከስልጣን አነሳች።

ቦታውን ቀደም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩት የኮሚኒስት ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ዋንግ ዪ ይያዛል ተብሏል።
የሚስተር ኪን ለረጅም ጊዜ ከሕዝብ እይታ መሰወር እና የሚኒስቴሩ ዝምታ ቁጣን አባብሷል። ባለፈው ታህሳስ ወር የተሾሙት ሚስተር ኪን የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ታማኝ ረዳት ሆነው ይታዩ ነበር።
“የቻይና ከፍተኛ የህግ አውጭ አካል ዋንግ ዪን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጎ ለመሾም ድምጽ ሰጥቷል” ሲል የመንግስት የዜና ወኪል ዢንዋ መናገሩን ቢቢሲ ዘግቧል። ሚስተር ኪን ከስልጣን የሚነሱበት ምክንያት አልተገለጸም ሪፖርቱ ግን ፕሬዝዳንት ዢ እርምጃውን የሚፈቅደውን
አዋጅ ፈርመዋል ብሏል።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc