
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia-የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሶማሌ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጀግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና የቅድመ ዝግጅትና የተማሪዎች አቀባበል ሁኔታን ተመልክተዋል።

በጉብኝታቸው የዩኒቨርሲቲውን አመራሮችና ተፈታኝ ተማሪዎችን ስለቅድመ ዝግጅቱ ያነጋገሩ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎችም ተረጋግተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ ማበራታታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሀምሌ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












