አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 18/2015 NBC Ethiopia- በካሜሮን በትላንትናው ዕለት ዱዋላ ከተማ በተከሰተው የህንጻ መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 34 ደርሷል፡፡

ባለ አራት ፎቅ ህንጻው ያለ ፍቃድ መገንባቱን የቤቶችና የከተማ ልማት ሚኒስትሩ ኬሌስቲን ኬቻ ኩረቴስ አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ አደጋው የደረሰበት ስፍራ ተገኝተው ህንጻው ያደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል፡፡ በደረሰው አደጋ 21 ሰዎች በጽኑ ቆስለው በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው ተብሏል፡፡
የነፍስ አድን ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ አሁን ላይ በህንጻው ፍርስራሽ ውስጥ ምንም የቀረ ሰው እንደሌለ ተረጋግጧል፡፡

እንዲህ አይነት አሳዛኝ አደጋ ዳግመኛ እንዳይከሰት የሀገሪቱ መንግስት የቤት ግንባታ ላይ የጥራት ቁጥጥር ሊያደረግ እንደሚገባ የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
በሀገሪቱ ውስጥ የመኖሪያ ቤቶችን የሚቆጣጠረው የካሜሩን የሲቪል መሐንዲሶች ትዕዛዝ ኃላፊ ኪዚቶ ንጎዋ “አሁን እንደዚህ አይነት አደጋዎች ለጥቂት ጊዜ ባላጋጠሙን ደስተኞች ነበርን ብለዋል፡፡
በከተማዋ ከ7 አመት በፊት አንድ ትልቅ ህንጻ በተመሳሳይ ሁኔታ መደርመሱ የሚታወስ ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc