አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 14/ 2015 NBC Ethiopia-አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ወይም ሰው ሰራሽ አስተወሎት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በህይወታችን ውስጥ ያላው ወሳኝ ሚና እየጨመረ መምጣቱ እየተነገረ ነው። ተጽእኖው ከሰው ልጅ ህልውና አልፎ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እና ዘርፎች ላይ በብዛት እየተስተዋለ ነው።

ከጤና እስከ ፋይናንስ፣ ከትራንስፖርት እስከ ንግድ ፣ ከትምህርት እስከ ዕለት ዕለት ድርጊታችን ድረስ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አኗኗራችን ብሎም የአሰራር መንገዳችንን እያሻሻለ ስለመሆኑ የማይካድ እውነት ከሆነ ሰንበት ብሏል፡፡ ይህም ህይወታችንን በማናስበው መንገድ ቀለል እያደረገው ነው።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሰዎችን ህይወት ቀላል የሚያደርግበት አንዱና ዋነኛው መንገድ አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ስራዎችን አውቶሜትድ በሆነ መለኩ በማዘጋጀት ነው። ለምሳሌ በንግድ ተቋማት ቻትቦቶች ለኩባያዎች የደንበኞችን ፍላጎትና የድጋፍ ጥያቄዎችን የማስተናገድኛ የመመለስ ስራን በመሸፈን የሰው ኃይል ወደ ሌሎች የስራ ዘርፎች እንዲሰማሩ ማስቻሉ ነው። በተመሳሳይ በማምረቻው ዘርፍ ሮቦቶች ለሰው ልጆች ፈታኝ እና አደገኛ የሆኑ የስራ ዘርፎችን እንዲሸፍኑ በማድረግ ምርታማነት እንዲጨምር እያደረጉ ነው።
በጤና አጠባበቀ ዘርፍ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታካሚ ውጤቶችን ለማሻሻል እና ወጪዎችን ለመቀነስ ጥቅም ላይ ይውላል። በተለይም በሜዲካል ኢሜጂንግ ቴክኖሎጂ እንደ ኤም.አር.አይ እና ሲቲ ስካን ምርመራዎች የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አልጎሪዝም በመጠቀም በሽታን እና በሰውነት ውስጥ ትክክለ ያልሆኑ ነገሮችን በከፍተኛ ጥራት መለየት ይችላሉ።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መኖሪያ ቤታችንን አእና ከተሞቻችንን ስማርት እና ለኑሮ አመቺ ያደርጋሉ። በመኖሪያ ቤት ውስጥ ሙቀትን እና የቤታችንን ብርሃን በምንፈልገው መጠን ማስተካከል ይችላሉ። በከተሞችም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የትራክ ፍሰትን መቆጣጠር እና ማስተካከል የህዝብን ደህንነት ማሻሻል ይችላል።

የትምህርተ ዘፍር አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ተጨባጭ ተጽእኖ እየፈጠረ ያለበት መስክ ነው። በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የመማሪያ መድረኮች ተማሪዎች በራሳቸው ዘይቤ እና ፍጥነት እንዲማሩ እየረዳቸው ነው ሲሆን፤ ግላዊ ግብረመልስ እና ምክሮችን ይሰጣሉ።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ጤናችን እና ደስታችንን ሊያሻሽሉ የሚችሉ መርሃግብሮችን እና አገልግሎቶቹን ለማበልጸግ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው።
በጥቅሉ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጆችን ህይወት በብዙ መልኩ እያቀለለው ነው። አድካሚ ስራዎችን በማቅለል፣ የጤና አጠባበቅን በማሻሻል፣ ቤታችንን እና ከተማችንን በማሳመር ወይም የኑሯችንን ጥራት በማሻሻል፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት የምንኖርበትን እና የምንሰራቀትን መንገድ አዘምኖታል። የሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተሻሻለ የሚሄድ መሆኑ ህይወታችንን ቀላል እና ምቹ ሊያደርጉ የሚችሉ ከዚህ የበለጠ ተጽዕኖ የሚፈጥሩ መተግበሪያዎች እንጠብቃለን። ከዚህ ጥቅም ባሻገር ደግሞ ጥቂት የማይባሉ ምሁራን ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰው ልጅን ለፈተና የሚዳርግ ነው በማለት የሚቃወሙ አልጠፉም፡፡እንደመረጃ ምንጭ አልጀዚራ እና ቢቢሲን ተጠቅመናል
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook-https://www.facebook.com/ethiopiannbc