
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 13 2015| NBC Ethiopia- የሩሲያው ቅጥረኛ ወታደራዊ ቡድን ዋግነር ወደ አፍሪካ ሀገራት ለዘመቻ ወታደሮቹን እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል። የቡድኑ መሪ ፕሪጎዥን ለተዋጊዎቹ ያስተላለፈበት የቪዲዮ ምስልም ተለቋል፡፡
የቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን መሪው ፕሪጎዥን ባስተላለፈው መልዕክት አጋሮቹን ላስመዘገቡት ድል አመስግኖ በዩክሬን ጦርነት እንደማይሳተፉና ለአፍሪካ ጉዞ ወታደሮቹን ተዘጋጁ ማለቱ ተሰምቷል።

የዋግነር ቅጥረኛ ወታደራዊ ቡድን እኤአ ከ2018 ጀምሮ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ሊቢያ እና ማሊ ተልዕኮ ወስዶ ሲንቀሳቀስ እንደነበር አልጀዚራ ዘግቧል ።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website –https://nbcethiopia.com/news/










