
አዲስ አበባ |ሐምሌ 13 2015| NBC Ethiopia – ፕሮጀክቱን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይና የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አለምፀሀይ ሽፈራው እና ሌሎች የመንግስት ስራ ሀላፊዎች መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
ለምረቃ የበቁት ፕሮጀክቶች ከ1ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተደርጎባቸው የተገነቡ 41 የካፒታል ፕሮጀክቶችና 24 ፕሮጀክቶች በህዝብ ተሳትፎ የተገነቡ በአጠቃላይ 65 ፕሮጀክቶች መሆናቸው ተገልጿል ።

ለምረቃ ከበቁት ፕሮጀክቶች መካከል ትምህርት ቤቶችና ትምህርት ቤት የአስተዳደር ሕንፃዎች፣ፖሊስ ጣቢያዎች፣ ጤና ጣቢያ፣የዳቦ ፋብሪካ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች እንዲሁም የአጸደ ህፃናት ት/ቤት ያካተቱ መሆናቸውን በምረቃው ወቅት ተገልጿል ።
በሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc