አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- ሰሜን ኮሪያ የአሜሪካ ባህር ሰርጓጅ የጦር መርከብ ደቡብ ኮሪያ ከደረሰች በኋላ ሁለት የባለስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች፤ አሜሪካም የሚሳይሎቹን መተኮስ መረጃ በመያዝ ከአጋሮቿ ጋር በመሆን እየመከረች መሆኑ ታውቋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ቡድን በበኩሉ ሰሜን ኮሪያ እንዲህ ዓይነት ትንኮሳ እንድታቆም አስጠንቅቋል ።
እንደ አልጀዚራ ዘገባ ሰሜን ኮሪያ በተደጋጋሚ የምታደርገው የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃት የተመድን ጸጥታ ምክር ቤት ደንብ የሚቃረንና እና በአጠቃላይ በኮሪያ ገፀ ምድር ረብሻ የሚያስከትል በመሆኑ አጥብቆ እንደሚያወግዝ መከላከያ ቡድኑ ገልጿል።
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc












