Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ምስራቅ አፍሪካ ላይ   የማያባራው አተካራ

July 19, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- ባሉፉት ሀምሳ ዓመታት ውስጥ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከነጻነት ጦርነት ጀምሮ በተለያዩ አስከፊ  ግጭቶች ውስጥ ገብተው  አመጽን፣ መገንጠልን፣ የጎሳ ጦርነትን  እንደ ባሕል ወርሰውታል  ይላሉ የፖለቲካ ምሁራን ፤በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ረሀብ ህይወትን አደጋ ላይ እየጣሉ ነው። በሱዳን ያለው ግጭት በብዙ ቦታዎች ደካማ የመንግስት አመራርን እያሳየ ነው።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በሕይወት ለመትረፍ አስቸኳይ መሠረታዊ ፍላጎት ያስፈልጋቸዋል ትላለች በዓለም አቀፍ የምግብ ባንክ ኔትወርክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነችው ዋንጅሩ ካሙ ሩተንበርግ    

በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሀገራት ቢያንስ ከ70 አመታት በፊት ባጋጠመው አስከፊ ድርቅ በአካባቢው እየተመለከቱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ባይኖር ኖሮ ይህ ሊሆን እንደማይችል ጥናቶች ያሳያሉ።

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ፤ ግጭት  እንደ ክረምት አሸን የሚፈለፈልበት፤ ድርቅ እስክስታ የሚወርድበት፤ ረሀብ የሚጠነክርበት፤ ጦርነት እንደ ዝናብ የሚርከፈከፍበት፤ ስደት ዓይኑን የማያነቅልበት ለውዝገብና ለንትርክ የተፈጠረ አካባቢ ነው ለዚህ እንደ ቁልፍ ምክንያት የሚቀርበው ድግሞ  ቀጠናው   የተወሳሰበ ታሪክ ያለበት በመሆኑ ነው  ይላሉ የፖለቲካ ሊቃውንት፡፡  የአህጉሪቱ ክፍል የአፍሪካ ቀንድ ክፍል  የሚባለው በተለዋዋጭ ፖለቲካና እና ተከታታይነት ባለቸው ግጭቶች ይታወቃል፡፡በዚህ ተለዋዋጭ ቀጠና ውስጥ ኢትዮጵያ፤ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን ይይዛል።

ታሪካዊ ቅራኔዎች ፣ የጎሳ ፤ ብሄር እና የሀይማኖት ልዩነት፤ የስልጣን ግብግብ፤ ቀኝ ገዥዎች ያሰመሩት የእሳት ድንበር  እና የሀብት ሽሚያን ጨምሮ በርካታ ምክንቶች  በአፍሪካ ቀንድ ግጭት እንዲስፋፋ  አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የአፍሪካ ቀንድ የተለያየ ቋንቋ እና ባህል ያላቸው ጎሳዎች ይገኙበታ። እነዚህ ልዩነቶች በፖለቲከኞች ቁማር  ወይም በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አለመመጣን በሚፈጠርበት ወቅት በጎሳዎች መካከል የፍላጎት  ግጭት እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ቀጣናው ለበርካታ አስርት አመታት በአምባገነን ስርአት፣ በእርስ በእርስ ግጭት እና ያልተረጋጋ መንግስት ያለበት በመሆኑ ይህን ክፍተት በመጠቀም በርካታ ታጣቂ ቡድኖች እንደልባቸው የሚፈነጩበት፤ ጉልበተኞች የሚፎክሩበት፤ ምዕራባውያን ለጥቅማቸው ሲሉ የታቀደ ሽብር የሚያደርጉበት ስለሆነ ለቀጠናው ሰላም ማጠር ጉል ሚና አላቸው ።

ለቀጠናው አለመረጋጋት እንደምክንያት የሚነሱ ጉዳዮች

1.የፖለቲካ አለመረጋጋት- በአፍሪካ ቀንድ ግጭት እንዲከሰት ከፍተኛ ሚና አለው። ደካማ የመንግስት መዋቅር፣ ሙስና እና አካታች የሆነ የፖለቲካ ስርአት አለመኖር እና የስልጣን ሽኩቻ መኖር ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የፖለቲካ መሪዎች ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ማስቀደማቸው ደግሞ  ውጥረቱን ከፍ ያደርገዋል።

2. ግጭት ለመፍታት የሚችሉ ውጤታማ ተቋማት እና ግጭት የሚፈታበት ስልት  ባለመኖሩ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ማምጣት አልተቻለም።

3 .የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ የሚደረግ ውድድር ሌላው በአፍሪካ ቀንድ የግጭት መንስኤ ነው። ክልሉ በውሃ ሃብት፣ ሊታረስ የሚችል መሬት እና ስትራቴጂካዊ የባህር መስመሮችን ጨምሮ በብዙ ጠቃሚ ሀብቶች ተለይቶ ይታወቃል። በእነዚህ ሀብቶች ላይ በተለይም ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የይገባኛል ጥያቄዎች እና የመጠቅለል ፍላጎቶች እንዲፈጠሩ በር ከፍቷል፤፤ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የግጭት ሽክርከሪት  ማስቆም  መሰረታዊ ችግሮችን ለማስወገድ  መፍትሄዎችን ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል ።

  ማጠቃለያ

መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ሁሉን አሳታፊ  የፖለቲካ ሥርዓት  መፍጠር እና ግጭቶችን በመከላከል፤  ለውይይት፣ ለእርቅ፤ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትንና ልማትን ማስፋፋት ፣ ድህነትን ቅነሳ ላይ መስራት እንዲሁም ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ርብርብ መደረግ አለበት። የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶችን መፍታት መረጋጋትን ለማስፈን እንዲሁም በህዝቦች መካከል አብሮነት እንዲሰፍን ይረዳል።

በቶማይ መኮንን      

ምንጭ  አልጀዚራ፣ ቢቢሲ

YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA

TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia

Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ጀመረ

Next Post

ከቱፓክ  ሻኩር ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻ አካሄደ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ከቱፓክ  ሻኩር ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻ አካሄደ

ከቱፓክ  ሻኩር ግድያ ጋር በተያያዘ ፖሊስ በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ፍተሻ አካሄደ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባላስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፏ ተገለፀ

ሰሜን ኮሪያ ሁለት ባላስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፏ ተገለፀ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?