አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- ባሉፉት ሀምሳ ዓመታት ውስጥ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ከነጻነት ጦርነት ጀምሮ በተለያዩ አስከፊ ግጭቶች ውስጥ ገብተው አመጽን፣ መገንጠልን፣ የጎሳ ጦርነትን እንደ ባሕል ወርሰውታል ይላሉ የፖለቲካ ምሁራን ፤በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ግጭት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና ረሀብ ህይወትን አደጋ ላይ እየጣሉ ነው። በሱዳን ያለው ግጭት በብዙ ቦታዎች ደካማ የመንግስት አመራርን እያሳየ ነው።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በሕይወት ለመትረፍ አስቸኳይ መሠረታዊ ፍላጎት ያስፈልጋቸዋል ትላለች በዓለም አቀፍ የምግብ ባንክ ኔትወርክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል የሆነችው ዋንጅሩ ካሙ ሩተንበርግ
በአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ሀገራት ቢያንስ ከ70 አመታት በፊት ባጋጠመው አስከፊ ድርቅ በአካባቢው እየተመለከቱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ባይኖር ኖሮ ይህ ሊሆን እንደማይችል ጥናቶች ያሳያሉ።

የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ፤ ግጭት እንደ ክረምት አሸን የሚፈለፈልበት፤ ድርቅ እስክስታ የሚወርድበት፤ ረሀብ የሚጠነክርበት፤ ጦርነት እንደ ዝናብ የሚርከፈከፍበት፤ ስደት ዓይኑን የማያነቅልበት ለውዝገብና ለንትርክ የተፈጠረ አካባቢ ነው ለዚህ እንደ ቁልፍ ምክንያት የሚቀርበው ድግሞ ቀጠናው የተወሳሰበ ታሪክ ያለበት በመሆኑ ነው ይላሉ የፖለቲካ ሊቃውንት፡፡ የአህጉሪቱ ክፍል የአፍሪካ ቀንድ ክፍል የሚባለው በተለዋዋጭ ፖለቲካና እና ተከታታይነት ባለቸው ግጭቶች ይታወቃል፡፡በዚህ ተለዋዋጭ ቀጠና ውስጥ ኢትዮጵያ፤ ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ጅቡቲ፤ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን ይይዛል።
ታሪካዊ ቅራኔዎች ፣ የጎሳ ፤ ብሄር እና የሀይማኖት ልዩነት፤ የስልጣን ግብግብ፤ ቀኝ ገዥዎች ያሰመሩት የእሳት ድንበር እና የሀብት ሽሚያን ጨምሮ በርካታ ምክንቶች በአፍሪካ ቀንድ ግጭት እንዲስፋፋ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

የአፍሪካ ቀንድ የተለያየ ቋንቋ እና ባህል ያላቸው ጎሳዎች ይገኙበታ። እነዚህ ልዩነቶች በፖለቲከኞች ቁማር ወይም በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አለመመጣን በሚፈጠርበት ወቅት በጎሳዎች መካከል የፍላጎት ግጭት እንዲቀሰቀስ ያደርጋሉ።
ከዚህ በተጨማሪም ቀጣናው ለበርካታ አስርት አመታት በአምባገነን ስርአት፣ በእርስ በእርስ ግጭት እና ያልተረጋጋ መንግስት ያለበት በመሆኑ ይህን ክፍተት በመጠቀም በርካታ ታጣቂ ቡድኖች እንደልባቸው የሚፈነጩበት፤ ጉልበተኞች የሚፎክሩበት፤ ምዕራባውያን ለጥቅማቸው ሲሉ የታቀደ ሽብር የሚያደርጉበት ስለሆነ ለቀጠናው ሰላም ማጠር ጉል ሚና አላቸው ።

ለቀጠናው አለመረጋጋት እንደምክንያት የሚነሱ ጉዳዮች
1.የፖለቲካ አለመረጋጋት- በአፍሪካ ቀንድ ግጭት እንዲከሰት ከፍተኛ ሚና አለው። ደካማ የመንግስት መዋቅር፣ ሙስና እና አካታች የሆነ የፖለቲካ ስርአት አለመኖር እና የስልጣን ሽኩቻ መኖር ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። የፖለቲካ መሪዎች ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ማስቀደማቸው ደግሞ ውጥረቱን ከፍ ያደርገዋል።
2. ግጭት ለመፍታት የሚችሉ ውጤታማ ተቋማት እና ግጭት የሚፈታበት ስልት ባለመኖሩ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ማምጣት አልተቻለም።
3 .የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ የሚደረግ ውድድር ሌላው በአፍሪካ ቀንድ የግጭት መንስኤ ነው። ክልሉ በውሃ ሃብት፣ ሊታረስ የሚችል መሬት እና ስትራቴጂካዊ የባህር መስመሮችን ጨምሮ በብዙ ጠቃሚ ሀብቶች ተለይቶ ይታወቃል። በእነዚህ ሀብቶች ላይ በተለይም ለድርቅ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የይገባኛል ጥያቄዎች እና የመጠቅለል ፍላጎቶች እንዲፈጠሩ በር ከፍቷል፤፤ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የግጭት ሽክርከሪት ማስቆም መሰረታዊ ችግሮችን ለማስወገድ መፍትሄዎችን ተግባራዊ ማድረግን ይጠይቃል ።

ማጠቃለያ
መልካም አስተዳደርን ማስፈን፣ ሁሉን አሳታፊ የፖለቲካ ሥርዓት መፍጠር እና ግጭቶችን በመከላከል፤ ለውይይት፣ ለእርቅ፤ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትንና ልማትን ማስፋፋት ፣ ድህነትን ቅነሳ ላይ መስራት እንዲሁም ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር ርብርብ መደረግ አለበት። የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልዩነቶችን መፍታት መረጋጋትን ለማስፈን እንዲሁም በህዝቦች መካከል አብሮነት እንዲሰፍን ይረዳል።

በቶማይ መኮንን
ምንጭ አልጀዚራ፣ ቢቢሲ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://www.facebook.com/ethiopiannbc












