አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA -በኬንያ የዓለም መጨረሻን በጾም ሲጠባበቁ በረሀብ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ400 በላይ መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል።

በኬንያ ደቡባዊ ምስራቅ በሚገኘው ሻካሆላ ጫካ ውስጥ ጉድ ኒውስ ኢንተርናሽናል ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች በረሀብ መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን በሚልም በሻካሆላ ጫካ ውስጥ ሲጠባበቁ የነበሩ ሲሆን ፣የተወሰኑት ለቀናት በመጾም በረሀብ ሲሞቱ ሌሎቹ ደግሞ በከፍተና ድብደባና በመታነቅ እንደሞቱ ተነግሯል።
በያዝነው ሳምንት ፖሊስ ሌላ ተጨማሪ 12 አስከሬኖችን ካገኘ በኋላም የሟቾች ቁጥር ከ400 በላይ መድረሱ ነው ቢቢሲ የዘገበው።
የዚህ እንቅስቃሴ መሪ ፖል ማኬንዚ የዓለም መጨረሻ እንደተቃረበ በመስበክ ተከታዮቹ ኢየሱስን ለማግኘት የሚችሉት በረሀብ ሲሞቱ እንደሆነ አሳምኗቸዋል ተብሏል። ፖል ማኬንዚ እስካሁን በይፋ አልተከሰሰም። ከዚህ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በረሀብ ከተረፉት መካከል 65ቱ ኬንያውያን ራስን በማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበባቸው መሆኑ ታውቋል ።
በሃና ተሰማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://nbcethiopia.com/news/












