አዲስ አበባ | ሐምሌ 12 2015 | NBC ETHIOPIA- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ዲፕሎማሲ ክንውኖችን አስመልክቶ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለሃገር የገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አለም አቀፍ አጀንዳ እየሆነ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ገለፁ። ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካ ጉዳይ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።
የአረንጓዴ ዲፕሎማሲና በኬንያ ናይሮቢ የተካሄደው 43ኛው የአስፈጻሚዎች ስብሰባ ስኬታማ ነበር ብለዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አለም አቀፍ አጀንዳ እየሆነ ነው። ከኢትዮጵያ ባሻገር የአፍሪካ ጉዳይ ስለመሆኑም ጠቁመው የአረንጓዴ አሻራ በአገር ደረጃ ታሪክ የተሰራበት ነውም ብለዋል።
ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ያደረጉ ኤምባሲዎች፣ አለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር መሳተፋቸውን ጠቅሰው ለተሳትፏቸውም ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የተባበሩት መንግስታት አጀንዳ እንደነበር አስታውሰዋል። በጥቅሉ አለም አቀፍ ተቀባይነት እያገኘ መንጣቱን ተናግረዋል። ።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ተጠናክሮ እንዲቀጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የገንዘብ ማፈላለግ ሃላፊነቱን እንደተወጣም ኢ ፕ ድ ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook –https://nbcethiopia.com/news/