
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳቡን የሚቃወሙ ምዕራባውያን ሀገራት በሙስሊሞች ቅዱስ ቁርኣን ላይ በቅርቡ የተፈጸሙ ጥቃቶችን አውግዟል።
ረቂቅ የውሳኔ ሃሳቡን 57 አባላት ያሉት የእስልምና ትብብር ድርጅት (ኦአይሲ) በመወከል ቀርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡ ቁርዓን ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን ለማውገዝ የሚጠይቅ እና “የሃይማኖት ጥላቻ ድርጊቶች” ሲል የገለፀው ሲሆን 47 አባላት ባሉት ምክር ቤት ነው።
የውሳኔ ሃሳቡ የፀደቀው በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት 53ኛ መደበኛ ጉባኤ 28 ሀገራት ድጋፍ፣ 12 ሀገራት ተቃውመውት እና 7 ሀገራት ድምፀ ተአቅቦ አድርገዋል።

የውሳኔ ሃሳቡን የድጋፍ ድምጽ የሰጡ ሀገራት አልጄሪያ፣ አርጀንቲና፣ ባንግላዲሽ፣ ቦሊቪያ፣ ካሜሩን፣ ቻይና፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኩባ፣ ኤርትራ፣ ጋቦን፣ ጋምቢያ፣ ህንድ፣ ካዛኪስታን፣ ኪርጊስታን፣ ማላዊ፣ ማሌዥያ፣ ማልዲቭስ፣ ሞሮኮ፣ ፓኪስታን፣ ኳታር ሴኔጋል፣ ሶማሊያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ዩክሬን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኡዝቤኪስታን እና ቬትናም ናቸው።
ቤልጅየም፣ ኮስታሪካ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሊትዌኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ሞንቴኔግሮ፣ ሮማኒያ፣ እንግሊዝ እና አሜሪካ ውሳኔውን ተቃውመዋል።
ቱርክ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ውስጥ የታዛቢነት ደረጃ ስላላት የመምረጥ መብት የላትም።
እንዲሁም ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩኤስ እና አንዳንድ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በሙስሊሙ ቅዱስ መጽሃፍ ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ተከትሎ ማክሰኞ በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ባደረጉት አስቸኳይ ክርክር የቁርኣንን ቃጠሎ አውግዘዋል።
በሃና ተሰማ
ምንጭ(አናዱሉ)
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc












