
አዲስ አበባ ሐምሌ 5 ፤ 2015 | NBC ETHIOPIA- ሐረር ከተማ ከሰሃራ በታች ካሉ ከተሞች የመጀመሪያዋ የዓለም ቅርስ ከተሞች ድርጅት (Organization of World Heritage Cities) አባል ከተማ ሆና ተመዝግባለች።
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪም በካናዳ ኩቢክ ከተማ በተካሄደው የፊርማ ስነ-ስርዓት ሐረር ከተማ የዓለም የቅርስ ከተሞች አባል ሆና የተመዘገበችበትን ፊርማ አኑረዋል።

ኢዜኣ እንዳስታወቀው ሐረር ከተማ 115 ሀገራትን በአባልነት በያዘው የቅርስ ከተሞች ድርጅት በፈረንጆች አቆጣጠር ከሰኔ ወር 2023 ጀምሮ ነው የተመዘገበችው።
ሐረር ከተማ ከዓለም የቅርስ ከተሞች መካከል አንዷ ሆና መመዝገቧ ከተማዋ ባህላዊና ታሪካዊ ቅርሶችን ለማልማት እና ለቱሪዝም ዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
ሐረር ከተማ የጁገል አለም አቀፍ ቅርስን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ አለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ ከተማ ከመሆኗ በተጨማሪ ከተማዋ ዜጎች በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የሚኖሩባት ከተማ በሚል በተባበሩት መንግስታት የሳይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም ዩኔስኮ እውቅና እንደተሰጣት ይታወሳል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia












