Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ኔቶ ለዩክሬን ተጨማሪ ጦር መሣሪያ ለማቀበል ወሰነ

February 23, 2023
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram
NATO Secretary General Jens Stoltenberg and the President of Ukraine Volodymyr Zelenskyy

አዲስ አበባ |የካቲት 16 2015 | NBC ETHIOPIA- የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት የሰሜን ቃል ኪዳን ድርጅት (NATO)አባል ሃገራትን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳስቧል። አንድ ዓመት ሊደፍን በተጠጋው ጦርነት ሩስያ በምሥራቃዊ ግንባሮች ድል እየተቀዳጀች መሆኑን በመናገር ላይ ናት። ሁኔታው ያሳሰባቸው የኔቶ አባል ሃገራት ባለፉት ሁለት ቀናት በብራስልስ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ስብሰባ ተቀምጠው ውሳኔ አሳልፈዋል።

በውሳኔያቸውም ለዩክሬን ተጨማሪ ጦር መሣሪያ በአፋጣኝ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል። የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ያንስ ሽቶልቴንበርግ፦ «ፕሬዚደንት ፑቲን ዩክሬን ውስጥ ድል ከተቀዳጁ ያ ለዩክሬን እጅግ አሳዛኝ ነው» ብለዋል። ያም ብቻ አይደለም ዋና ጸሐፊው፦ «ለእኛም አደገኛ ነው» ሲሉ ተደምጠዋል። 

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ዓባል አገሮች የመከላከያ ሚኒስትሮች፤ ባለፉት ሁለት ቀናት በብራስልስ የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ባካሄዱት ስብሰባ፤ የድርጅቱን የመከላከያ ብቃት ለማሳደግና ለማጠናከር የሚያስችሉ ርምጃዎችን ለመውስድና ለዩክሬን ተጨማሪ የጦር መሣሪያና ተተኳሾች እርዳታዎችን በብዛትና በፍጥነት ለማድረስ ወስነዋል። የሰላሳዎቹ የኔቶ አባል አገሮችና የሌሎች ሀያ ዩክሬንን ለመርዳት ከድርጅቱ ጋር የተጣመሩ ሀይሎች ሚኒስትሮች በጋራ የተሰበሰቡት፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የተጠናከረ ጥቃት ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሆነችና፤ ዩክሬን ባንጻሩ ቃል የተገባላትን የጦር መሳሪያ በጇ ስታስገባና እንደውም የተተኳሽ እጥረት እንዳጋጠማት እየተገለጸ  ባለበት ወቅት ነው።፡ በዩክሬን እይተካሄደ  ያለው ጦርነት በአውሮጳ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ያልታየ  አውዳሚ  ጦርነት እንደሆነ ነው በብዙዎች እየተገለጸ ያለው። ያም ሆኖ አሁንም የሰላም ጭላንጭል እየታየ እንዳልሆነና ይልቁንም ሩሲያ ጥቃቷን አጠናክራ የቀጠለች መሆኑን የገለጹት  የኔቶ ዋና ጸሐፊ ሚስተር ያንስ ስቶልቴንበርግ፤ የሚኒስትሮቹን ስብሰባ ትኩረትና ያሳለፏቸውን ውሳኔዎች በጋዚጣዊ መግለጫቸው አብራርተዋል፤ “ ለዩክሬን  የሚሰጠውን እርዳታ ማጠናከርና ማሳደግ፤  የመከላከል አቅማችንና ብቃታችን በአስፈላጊው ሀይልና ትጥቅ እንዲገነባ ማድረግ፤ የወታደራዊ መሰረታዊ ልማቶችን ማጠናከርና ከእንዱስትሪዎቻችን ጋር ማጣመር” የመሳሰሉት ዋናዋናዎቹ ውሳኔ የተላለፈባቸው አጀንዳዎች እንደሆኑ ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው፤ ዩክሬን በጦርነቱ የምትጠቀመው የተተኳሽ መጠን አባል አገሮች ከሚያመርቱት በላይ በመሆኑ ይህንን ክፍተትና እጥረት ለማሟላት የመሳሪያ እንዱስትሪዎችን ማንቀስቀስና አዳዲሶችም እንዲከፈቱ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል። ሚኒስትሮቹ ለዩክሬን ባስቸኳይ የተተኳሾችና የሎጂስቲክስ አቅርቦት እንዲደርስ መስማማታቸውን ያወደሱት ዋና ጸሐፊ ስቶልቴንበርግ፤ የኔቶን የመከላከል አቅምና ብቃት ለማጠናከር የሚያስችሉ እርምጃዎችን መውሰድ አስፈላጊ የሆኑባቸው ምክኒያቶች፤ «የሩሲያ የጦረኝነት ባህሪ፣ የአሸባሪዎች የጥቃት ስጋትና ከቻይና እየተቃጡ ያሉ ፈተናዎች ናቸው» በማለት፤ ይህም ምን ያህል ዓለም በአደገኛ ሁኒታ እንዳለች የሚያሳይ ነው ብለዋል። ከዚሁ ጋርም ሚኒስትሮቹ የመሳሪያ ኢንዱስትሪዎቻቸውን ማጎልበትና አዳዲሶችንም ማቋቋም እንደሚያስፈግ እንዲሁም የመከላከያ በጅታቸውን ከጠቅላላ ገቢያቸው ቢያንስ ከሁለት ከመቶ በላይ ማሳደግ እዳለባቸው መስማማማታቸው ተገልጿል።

የኔቶ አባል አገሮችና አጋሮቻቸው እስካሁን ለዩክሬን በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ እንደረዱ የሚገለጽ ሲሆን፤ አንድ መንግስታዊ ያልሆን የጀርመን ድርጅት እንደገለጸው፤ የኔቶ አባል አገሮች ባለፈው አንድ አመት ብቻ ለዩክሬን 75.2 ቢሊዮን ዩሮ የፋይናንስ፤ ሰባዊና ወታደራዊ እርዳታ ለግሰዋልል። ይሁን እንጂ ለዩክሬን የሚሰጠው እርዳታና በገፍ እየቀረበ ያለው የጦር መሳሪያ፤ ሩሲያ ጦርነቱን እንድታቆም ከማስገደድና ሰላም እንዲሰፍን ከማድረግ ይልቅ፤ የጦርነቱ አድማስ እንዳያሰፋውና እልቂት ውድመቱም እንዲጨምር እንዳያደርገው ያሰጋል ነው የሚባለው። በኔቶው ስብሰባ የተገኙት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስተር ሚስተር ሊዮድ ጀምስ ኦውስቲን እንደሚሉት ግን ፤ የኔቶና አጋሮቹ እምንት፤ የዩክሬንን አቅም በሁለንተናዊ መልኩ መገንባትና ማሳደግ ከተቻለ፤ የጦርነቱ ሁኒታ እንደሚለወጥ ነው። «አላማችን ለዩክሬኖች ተጨማሪ አቅም በመሰጠትና በመርዳት በጦርነቱ አጥጋቢ ውጤት እንዲያገኙና ወሳኝ ሚና እንዲኖራቸው ማስቻል ነው» በማለት ይህ ከሆነ ዩክሬኖች በጦርነቱ ትልቅ ለውጥ ለማምጣት እድል እንደሚኖራቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ሩሲያ ምዕራባውያን ለዩክሬን በገፍ የጦር መሳሪያ በማቅረብና በመርዳት የጦርነቱ አካል ሁነዋል በማለት ከመክሰስ አልፎ፤ እየደረሰ ላለው እልቂትና ውድመት ተጠያቂዎችም እንደሆኑ ትገልጻለች። በእርግጥም ኔቶ ይህን ያህል መሳሪያ እያቀረበና ተዋጊ ጀቶችንም ለማቅረብ እያሰበ ከሆነ፤ የጦርነቱ አካል አልሆነም ማለት ይቻላል ወይ? ተብለው የተጠይቁት ዋና ጸሀፊ ስቶልቴንበርግ “ኔቶም ሆነ የኔቶ አጋሮች የጦርነቱ አካል አይደሉም። እያደርግን ያለነው እራሷን እየተካላከለች ያለችውን ዩክሬንን መርዳት ነው። ይህን የማድረግ መብትም አለን በማለት የሚቀርብባቸውን ክስ አስተባብለዋል።

የአውሮፓ ኅብረትና ኔቶ ዩኪሬንን ከመርዳት ባለፈ በሩሲያ ላይ በርካታ የማዕቀብ ውሳኔዎችን ማሳለፋቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሰሞኑን ደግሞ አስረኛውን የማዕቀብ ውስኔ ለማሳለፍ በዝግጅት ላይ እንደሆኑ እተገለጸ ነው።

#NBC_ETHIOPIA

#ሆኖ_መገኘት

ShareTweetShare
Previous Post

አንድ አመት ሊሞላው አንድ ቀን የቀረው ጦርነት

Next Post

እስራኤል በጋዛ የአየር ድብደባ ጀመረች

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post

እስራኤል በጋዛ የአየር ድብደባ ጀመረች

ለሰውነታችን ጠቃሚ የአትክልት አያነቶች

የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት- ቁልፍ ክንውኖች በ366 ቀን ላይ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?