

የአዲስ አበባ |የካቲት 13 2015 | NBC ETHIOPIA- በ36ኛው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ የአገራት መሪዎች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ወደ አገራቸው እየተመለሱ ነው፡፡
መሪዎቹ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በአህጉራዊውን ነጻ የንግድ ቀጣና እና በርካታ የሁለትዮሽ ውይይቶችን ማድረጋቸው ይታወቃል።
በተጠናቀቀው 36ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ድርቅን መቋቋም እንዲሁም የጤና ጉዳዮች መሪዎች ከመከሩባቸው ጉዳዮች መካከል መሆናቸው ይታወቃል።

በአዲስ አበባ የነበራቸውን ቆይታ ያጠናቀቁት መሪዎች ዛሬም ከማለዳው ጀምሮ ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው።
በዚህም የናሚቢያ፣ ሴራሊዮን፣ ሌሴቶ፣ ቦትስዋና፣ ቡሩንዲ እና ሲሼልስ መሪዎች ዛሬ ማለዳ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ፕሮቶኮል ሹም አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ሸኝተዋቸዋል።
በመሪዎቹ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ ሌሎች መሪዎችም ዛሬ እስከ አመሻሽ ድረስ ወደ አገራቸው እንደሚያቀኑ ይጠበቃል።

ከትናንት ማታ ጀምሮም የሞዛምቢክ፣ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ የኬኒያ፣ የሩዋንዳ፣ የሞሮኮ፣ የማዳጋስካር እንዲሁም የሴንትራል አፍሪካ ሪፐብሊክ መሪዎች ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የዚምባብዌ ፣አንጎላ ፣ደቡብ አፍሪካ ፣ኮንጎ ብራዛቢል፣ቻድ፣ ጋና እና ዩጋንዳ መሪዎች ከተመለሱት መካከል ናቸው።
ሃና ተሰማ
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት









