
የአዲስ አበባ |የካቲት 13 2015 | NBC ETHIOPIA-የብራዚል የሳኦ ፓውሎ ግዛት ባለስልጣናት በከባድ ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት ቢያንስ 36 ሰዎች መሞታቸውን አንዳንድ ከተሞች ዓመታዊ የካርኒቫል በዓላትን እንዲሰርዙ እዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎች ከ600mm (23.6inch) በላይ ዝናብ እንደጣለ እና ይህም ለወሩ ከሚጠበቀው መጠን በእጥፍ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግባል።
የነፍስ አድን ቡድኖች የተረፉትን ለማግኘት እና መንገዶችን ለመክፈት ሲታገሉ ቆይተዋል። “የፍለጋ እና የነፍስ አድን ቡድኖች ወደ ብዙ ቦታዎች ለመድረስ እየቻሉ አይደለም፤ የተመሰቃቀለ ሁኔታ ነው” ሲሉ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የሳኦ ሴባስቲአኦ ከተማ ከንቲባ ፌሊፔ አውጉስቶ ተናግረዋል።
ሚስተር አውጉስቶ አክለው የጉዳቱን መጠን እስካሁን አልገመትነውም፤ ተጎጂዎችን ለመታደግ እየሞከሩ እንደሆነ እና በከተማዋ በደርዘን የሚቆጠሩ ጠፍተዋል እና ወደ 50 የሚጠጉ ቤቶች ፈርሰዋል ሲሉ ሁኔታው እጅግ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

በደረሰው አደጋ 228 ሰዎች ቤት አልባ ሆነው 338 ሰዎች ከሳኦ ፓውሎ በስተሰሜን ከሚገኙ የባህር ዳርቻዎች እንዲወጡ ተደርጎል፡፡
ፕሬዝዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ “ሁሉንም የመንግስት እርከኖች አንድ ላይ ሰብስበን በህብረተሰቡ ትብብር የቆሰሉትን እናክማለን ፣የአውራጃ መንገዶችን ፣የኃይል ግንኙነቶችን እና የቴሌኮሙኒኬሽን ስራዎችን እንሰራለን በዚህ አደጋ ዘመዶቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች መጽናናትን እመኛለሁ።” ሲሎ ሀዘናቸውን ገልፀዋል፡፡
የላቲን አሜሪካ ትልቁ የሳንቶስ ወደብ የንፋስ ፍጥነት በሰአት 55 ኪሜ በሰአት (34mph) በመብለጡ እና ሞገዶች ከአንድ ሜትር በላይ መውጣታቸው የሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
በአካባቢው ተጨማሪ ከባድ ዝናብ ሊጥል ይችላል, ይህም ለአደጋ ጊዜ ቡድኖች ሁኔታውን የበለጠ የከፋ ያደርገዋል፡፡ ባለፈው አመት በደቡብ ምስራቅ ፔትሮፖሊስ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ከ230 በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል።
ሃና ተሰማ
ምንጭ(ቢቢሲ)
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት